制作
出演艺人
Abdu Kiar
表演者
作曲和作词
Dawit Tilahun
词曲作者
歌词
ወይ ሸገር ወይ ሸገር ስንቱ በሷ አዘነ
ታሪካዊው ፍቅሯ ሂሳባዊ ሆነ
አንድ'ና አንድ ሁለት ሂሳቡ ግልፅ ነው
ያ'ራዳ እናትነት ሲኖርህ ብቻ ነው
አራዳ... ስንቱን ሰብስባ፤
አራዳ... ፍቅር ያስተማረች
አራዳ... የሸገር ንግስት፤
አራዳ... እናት ነበረች
አራዳ... በነበር ቢሆን
አራዳ... በነበር'ማ
አራዳ... ያበሻ ጆሮ
አራዳ... ችግር ባልሰማ
እኔ አላማረኝም አዲስ ነገር በዝቷል
በኪስህ ተማመን ጎበዝ ፍቅር ጠፍቷል
ይዞ መገኘት ነው ትልቁ ጨዋታ
በል እ'ዳላፍርብህ ያራዳ ልጅ በርታ
መብላት መጠጣቱ ተፋቅሮ
ደጃች ውቤ ቀረ ድሮ
ያብሮ መብላት ተሳስቦ ኑሮ
ገዳም ሰፈር ቀረ ድሮ
መብላት መጠጣቱ ተፋቅሮ
ደጃች ውቤ ቀረ ድሮ
ያብሮ መብላት ተሳስቦ ኑሮ
ገዳም ሰፈር ቀረ ድሮ
ነበረ ነበረ ምን ይጠቅማል ወሬ
በድሮ በሬማ አይታረስም ዛሬ
እንኳን ካ'ባት ካ'ያት በሂደት የመጣ
ጠዋት ያስቀመጡት መች ይገኛል ማታ
ድሮማ... ያለ ጠገራ
ድሮማ... መሃል ሸገር
ድሮማ... የትም የማይገኝ
ድሮማ... ፍቅር ነበር
በነበር... በነበር ቢሆን
በነበር... በነበር'ማ
በነበር... ያ'በሻ ጆሮ
በነበር... ችግር ባልሰማ
እኔ አላማረኝም ዘንድሮ ሌላ ነው
ህይወት ላለው እንጂ አይሆን ለነበረው
ይዞ መገኘት ነው ትልቁ ጨዋታ
በል እንዳላፍርብህ ያራዳ ልጅ በርታ
ያራዳ ልጅ በርታ ዘንድሮ
ፍቅርማ ቀረ ድሮ
ያራዳ ልጅ በርታ ዘንድሮ
የድንጋይ ኳስ ቀረ ድሮ
Written by: Dawit Tilahun