歌詞

የብርሃን ሰልፍ ነው ያነገተ ፍቅር ሰላም ጤና ለአዳም እንኳን ሰው እንስሳም የፍቅር ነው ሰራዊቱ ዱር አራዊቱ ምን አስተከዘህ ከሃዘን ዋሻው የኔ ሆድ ባሻው ባሻው ይደሰት ልብህ ከቶም እንዳይከፋው አዝነህ ላትገፋው ቢከፋም ቢለማም ያለም ኑሮህ ምን ባይቀና ሁን አንተ ጤና ቸር አስብበት በሰጠህ እድሜ አይዞህ ወንድሜ ድንገት ቢከፋህ ባይቀናህ ኑሮ በዚህች ዓለም ጊዜ የማይፈታው ምንም የለም ጊዜም አሁን ነው ትናንት ሆኖ ቀሪ የነገው ቀን ሰሪ ዓመት ያህላል ቀን እየዞረ ዛሬም እራሱ ነገ ነበረ የጊዜ ሚዛን አይላወስም ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም ሳዝን አልውልም ሳላውቅ ማደሬን የኔ ነው በቃ አልሰጥም ዛሬን አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ ባሻው ይደሰት ልብሽ ከቶም እንዳይከፋው አዝኖ ላይገፋው ቢከፋም ቢለማም የዓለም ኑሮሽ ምን ባይቀና ሰርክ አንቺ ደህና ፍቅርን ሳይበት ኑሪና በዓለም አንቺ የእናት ቀለም ቀኑ ቢመሻሽ ብለሽ አትስጊ ፋኖስ የለም ፀሃይ ነሽና ለዚች ዓለም ዛሬን አብሪበት ለኩሺና ተስፋ ነገም እንዳይጠፋ ዓመት ያህላል ቀን እየዞረ ዛሬም እራሱ ነገ ነበረ የጊዜ ሚዛን አይላወስም ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም ሳዝን አልውልም ሳላውቅ ማደሬን የኔ ነው በቃ አልሰጥም ዛሬን አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ አይዞህ ልቤ አይዞህ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out