歌詞

እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ውበት ፡ ሞገስ ፡ ዘውድ ፡ አክሊሌ (፪x) ከቶ ፡ የማይርቅ ፡ በፍፁም ፡ ከአጠገቤ ሚራራልኝ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ አይጓደል ፡ በፍፁም ፡ ምሥጋናዉ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው በቅዱሳን ፡ ጉባኤ ፡ ህብረት ፡ መሆን ሊመሰገን ፡ ሊከብር ፡ ይገባዋል መልካም ፡ መዓዛ ፡ ሆኖ ፡ ያርግ ፡ መሥዋዕቴ ለወደደኝ ፡ አፍቃሪ ፡ መድሃኒቴ ይድመቅ ፡ ጭብጨባው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታውም ፡ ይሰማ ምሥጋና ፡ በአሪያም ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና (፪x) የአገኘሁት ፡ ደህንነት ፡ ለመንፈሴ ዳግም ፡ ልደት ፡ በደሙ ፡ መቀደሴ የአምላክ ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ አድርጐኛል ባመሰግን ፡ ብዘምር ፡ ያንስብናል ኦ ፡ ትበል ፡ ዛሬ ፡ ነፍሴ ታምጣ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ውዳሴ ፡ ለንጉሡ ጌታ ፡ ድንቅ ፡ ነውና (፪x) እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ውበት ፡ ሞገስ ፡ ዘውድ ፡ አክሊሌ (፪x) ከቶ ፡ የማይርቅ ፡ በፍፁም ፡ ከአጠገቤ ሚራራልኝ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ አይጓደል ፡ በፍፁም ፡ ምሥጋናዉ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው ይዘምራል ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ ፡ እያለ በአምላኩ ፡ ሰው ፡ መሆኑን ፡ ያስተዋለ ሕይወት ፡ የለውም ፡ ከጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሌላ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ክርስቶስ ፡ የእርሱ ፡ ተድላ ይድመቅ ፡ ጭብጨባው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታውም ፡ ይሰማ ምሥጋና ፡ በአሪያም ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና (፪x)
Writer(s): Daniel Amdemariam Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out