Lyrics

ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ የድንገት ትውውቅ የምሽት የማታ አሄ ሸለመኝ ለፍቅር የአንድ ቀን ሰላምታ አሄ የልቤ ምግብ ነው ሳቅና ጨዋታሽ ደስታና ፈገግታሽ እንደ ጥልፍ አጣፊ እንደ ኩታ ለባሽ አሄ ጥበቡን ደርቦ ማን ከሆዴ አስገባሽ አሄ በፍቅር መንገድ ላይ ይከፋል ትዝታ ነይ ነይ የኔ አውታታ ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ ሽመላማው ገላ ፍቅሯን እያደለኝ አሄ ተሸነፈ ልቤ እያደረ ጣለኝ አሄ ቢያሸበርቅ ነው ወይ ቢደራ ገላሽ አንጀቴን በላሽ ነገር አያቀና እኔማ ብልሃቴ አሄ ሰው ባፈቅር ከዳኝ ድፍን አካላቴ አሄ ማተቤን ለፍቅር በጥሼው ካንገቴ ናፍቆት ሆነ ዕርስቴ ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ በታጎለ ጉዞሽ የመለያየቱ ኡሁ ልቤ ሰው አይሸኝም አይችልም አንጀቱ አሄ ምነው ብቸኝነት ግዞት ያለ ዳኛ ነይልኝ እይኛ ልቤም ልቡን ካጣ ሆዴም ሆድ ከባሰው አሄ ናፍቆት ቀንበር ጠምዶ አንጀቴን ካረሰው አሄ እርሜን ላውጣ እንግዲ ወዳጅ ከተለየው ማጣት የታደለኝ እርሜን ላውጣ እንግዲ ወዳጅ ከተለየው ማጣት የታደለኝ
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out