Lyrics

ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ጥቁሯ ወርቅ ቀጥ እንደ ሸምበቆ አኳኋኗ በአታሞ ምት ረቆ ፍቅር ሲሞቅ እሳት ነዶ ማታ ውበት አየሁ ዳንኪራ ሲመታ ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ ናት የባሮ ቶም ሰርታ በዣንጥላው ብረት በጨረቃ ፍቅርን ያዜምንበት የታንኳው ላይ የወንዙ ሽርሽር እረፍት አጣው ትዝ ባለኝ ቁጥር ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ ናት የባሮ ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ መሸት ሲል ጀምበር አዘቅዝቆ ቀዩን ሰማይ ውሃው አንፀባርቆ እያየኋት በጨረቃ መብራት አማረኝ የታንኳ ላይ እራት ጉድ አረገኝ በውበት ሳር አስሮ አዬ ባሮ ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ ይሄ ልቤ የሆነብኝ ምነው ሀሳቤ ሁሌ ከአዊሊ ነው ልያት እንጂ ወይ ሄጄ ዳግመኛ ባደርጋት የሁሌ ጓደኛ ዓሳ ሆኖ ልኮኝ እንጀራዬ ከአዲስ አበባው የትውልድ አምባዬ ተመለስኩኝ በፍቅሯ ተይዤ የሸገር ልጅ ባዶ ቅርጫት ይዤ ኚላል ባድ ኦፔኖ አገነ ገቲያ ኚላል ባድ ኦፔኖ አነ ሚየጎ ኚላል ባድ ኦፔኖ አጀሎዬ ኚላል ባድ ኦፔኖ ናት ባሮ አሳ አጠምድ ብሎ ናት ባሮ ዘርግቶት መረቡን ናት ባሮ እንዴት ለቆንጆ ሴት ናት ባሮ ሰው ይጥላል ልቡን ናት ባሮ ዓይኔ እሷ ላይ ቀርቶ ናት ባሮ ዓሳ አጣሁ ለእራቴ ናት ባሮ ባዶ ቅርጫት ይዤ ናት ባሮ ተመለስኩኝ ቤቴ ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ ኚላል ባድ ኦፔኖ አገነ ገቲያ ኚላል ባድ ኦፔኖ አነ ሚየጎ ኚላል ባድ ኦፔኖ አጀሎዬ ኚላል ባድ ኦፔኖ ኚላል ባድ ኦፔኖ አገነ ገቲያ ኚላል ባድ ኦፔኖ አነ ሚየጎ ኚላል ባድ ኦፔኖ አጀሎዬ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out