Music Video

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Bereket Tesfaye
Bereket Tesfaye
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Bereket Tesfaye
Bereket Tesfaye
Songwriter

Lyrics

ብዙ ፍጥረት ያለው ባህር ውቅያኖሱ ለየብስ ሩብ ሰጥቶ ቀሪውን መልበሱ ላጥፋ ካለ አጥፊ ጡንቻ አለው ፈርጣማ ካንዱ ጌታ በቀር ማንንም አይሰማ ጥም አርኪ ይመስላል ግን ለጠማው ደሃ ውስጡ ስለሌለው ለመጠጥ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ ሰነፍ መርከበኛ ውቅያኖሱ ዳር ሚጠጣውን ሳይዝ መጓዝ ቢጀምር ውሃ መሃል ደርሶ ውሃ ይጠማዋል ውሃ በረሃ ላይ በውሃ ጥም ይሞታል አንድ ጉድጓድ አለች በጣም ትንሽዬ ህፃን ነህ አዋቂ ጨዋ ነህ ዱርዬ ሳትል ሳታዳላ ሁሉን ታጠጣለች ይህን ንፁህ ውሃ ታመነጨዋለች ጠቢቡ ገበሬ እሷ ዳር ይዘራል ዘሩም ምንጯን ነክቶ ማን ደርቆ ይቀራል ጌታ ኢየሱስን በዕምነቱ የነካ ከህይወት ውሃ ምንጭ ጠጥቶ እረካ ስንት ምስኪን አለ ሳይተኛ ሚያነጋ ነፍሱ ምትገረፍ በጥማት አለንጋ እግዚአብሔር ነፍሱን ነይ ላርካሽ ቢላት የእግዚአብሔርን ሳይሆን ለነፍሱ ሆዱን ሰማላት ጌታ በሌለበት በዛ ባዶ ቦታ ምኑንም ቢከቱ አይሰጥም እርካታ ሰማይ እና ምድር ባንዴ ተጠቅልሎ የኢየሱስን ቦታ አይሞላውም ችሎ የተከበበ በማይጠጣ በዓለም ያለ ሰው ኢየሱስን ያጣ በጀልባ እንደጠፋ ውቅያኖስ ላይ ኢየሱስ የሌለው ሰው እሱ አይደል ወይ ተበልቶ ተጠጥቶ የለም እርካታ ኑሮ ማለት ሃሩር ከሌለው ጌታ ኦ (ዳግመኛ አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው) (ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው) አልጠማኝ እኔ አልጠማኝም(ዳግመኛ አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው) (ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው)
Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out