Music Video
Top Songs By Haileye Taddesse
Credits
PERFORMING ARTISTS
Haileye Taddesse
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Elias Melka
Songwriter
Lyrics
እመኛለሁ
ሰው ይመኛል መቼም በድሜ እስካለ
ሁሉም ነገር ሚሆን እሱ እንዳለ
እስከመቼ በሃሳብ ሃዝኜ እዘልቃለሁ
እንደው ልፋ ቢለኝ እመኛለሁ
እመኛለሁ ሰው ይመኛል መቼም በድሜ እስካለ ሁሉ ነገር ሚሆን እሱ እንዳለ
እስከመቼ በሃሳብ ሃዝኜ እዘልቃለሁ
እንደው ልፋ ቢለኝ እመኛለሁ
ከነገ ዛሬ ስል እንዲሳካ ኑሮ
ቋጥሮ ጠብ ላይል ካምናው ለዘንድሮ
እድሌ ሊወሰን በፈጠረኝ ጌታ
አሰብኩኝ ጥዋት ማታ
ብዙ በመመኘት ጊዜ እንደማጣቴ
ተራራውን ሜዳ ያደርጋል ምኞቴ
ልብን እያስመኙ ስላሳጡት ሰላም
ይህች አለም አትሞላም
እድሌ ሊወሰን በፈጠረኝ ጌታ
አሰብኩኝ ጥዋት ማታ
እመኛለሁ
ሰው ይመኛል መቼም በእድሜ እስካለ
ሁሉ ነገር ሚሆን እሱ እንዳለ
እስከመቼ በሃሳብ ሃዝኜ እዘልቃለሁ
እንደው ልፋ ቢለኝ እመኛለሁ
እመኛለሁ
ሰው ይመኛል መቼም በድሜ እስካለ
ሁሉ ነገር ሚሆን እሱ እንዳለ
እስከመቼ በሃሳብ ሃዝኜ እዘልቃለሁ
እንደው ልፋ ቢለኝ እመኛለሁ
በሂወት እስትፋስ እስካለሁ በቁሜ
ይፈታል እያልኩኝ እንቆቅልሽ ህልሜ
አሁን ምን ሊሳካ በሃሳብ መንጎድ
ያለሱ ፈቃድ
መቼም ሰው ነኝና ስመኝ እኖራለሁ
ለሚሆን ለማይሆን እብከነከናከሁ
ተረቱም እንዲያ ነው የሰውልጅ ያልማል
አምላክ ይፈጽማል
አሁን ምን ሊሳካ በሃሳብ መንጎድ
ያለሱ ፈቃድ
እድሌ ሊወሰን በፈጠረኝ ጌታ
አሰብኩኝ ጧት ማታ
እድሌ ሊወሰን በፈጠረኝ ጌታ
አሰብኩኝ ጧት ማታ
እድሌ ሊወሰን በፈጠረኝ ጌታ
አሰብኩኝ ጧት ማታ
እድሌ ሊወሰን በፈጠረኝ ጌታ
አሰብኩኝ ጧት ማታ
Writer(s): Elias Melka
Lyrics powered by www.musixmatch.com