Lyrics

ምነው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር ሸንጎ የለም ባገር እንደው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር ሸንጎ የለም ባገር ሲጫን መሄጃሽ ሰረገላ አዳክመሽዋል የኔን ገላ በአዋጅ ይነገር ሰው ይጠራ ይፋ ይወጣል ያንቺም ስራ ምነው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር ሸንጎ የለም ባገር እንደው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር ሸንጎ የለም ባገር ጠዋት ተጫውተን ሳጣሽ ማታ ባሳብ አደርኩኝ በትዝታ ጨዋ አንቺ ካለሽ ባገሩ ላይ አጣፍጪው ፍቅርን ከዚም በላይ ዘመናይ እቅፍም አልልሽ ዘመናይ ልልበስሽ ሌት ተቀን ዘመናይ ብርዱ እንዴት ይውጣልኝ ዘመናይ እንዲህ ተራርቀን ዘመናይ ዳኛው ተሰይሞ ዘመናይ ባስቻለበት ቦታ ዘመናይ አገኝሽ ይሆን ወይ ዘመናይ ባቀርብ አቤቱታ ፍርድ አይወድም እንዴት ይባላል ሰው ለዚህ አይደል ወይ ካባስ የለበሰው ባዳባባይ ሀገሩን ሲዳኘው ህጉ አይደል ወይ ወቶ ያልተገኘው ያፍቃሪ ጡር እንዲታወቅለት ለመካሻው እንዲረቀቅለት በነጋሪት ይውጣለት አዋጅ ፍትህ አጥቶ እንዳይቀር ወዳጅ አልጋው ጭር አለ ክፍሉ ቀዝቅዞት እሱም እንደኔ ትካዜ ገብቶት ተበደልኩኝ ብል ምን አመጣለው በምን ከስሼ አስቀጣሻለው አልጋው ጭር አለ ክፍሉ ቀዝቅዞት እሱም እንደኔ ትካዜ ገብቶት ተበደልኩኝ ብል ምን አመጣለው በምን ከስሼ አስቀጣሻለው ምነው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር ሸንጎ የለም ባገር እንደው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር ሸንጎ የለም ባገር ሲጫን መሄጃሽ ሰረገላ አዳክመሽዋል የኔን ገላ በአዋጅ ይነገር ሰው ይጠራ ይፋ ይወጣል ያንቺም ስራ ዘመናይ ሹም አለምንብሽ ዘመናይ አንጥፌው ኩታዬን ዘመናይ በምን ልገላገል ዘመናይ ይሄን ትዝታዬን ዘመናይ ናፍቄሽ ስጎዳ ዘመናይ ፍቅርሽ ትዝ እያለኝ ዘመናይ አቤትም ብልብሽ ዘመናይ ባንቺ ፍትህ የለኝ ዘውትር ካይኔ ካጠገቤ ሳጣሽ በምን ዳኛ ጠይቄ ላስቀጣሽ ልቤ በሀሳብ ችሎት ይደር እንጂ በፍቅር ላይ የታለ ካስጠየቀሽ የኔማ ትካዜ በህልሜ ነሽ ተዳኘሽ ጊዜ ይግባኝ ብትይ መች ይቀበልሻል ይሄ ሳይጎልበት መች እሺ ይልሻል ብከራከርሽ ይዜ ጠበቃ በፍቅር ጉዳይ ለድል አልበቃ ስንስማማ እንጂ የእኛ ደስታችን አንጠቀምም በሙግታችን ስትከተዪው የራቅሽን እውነት አዳክመሽዋል የኔን ሰውነት በመተው መብትሽ ስትጠቀሚ ርቀሽ እየሄድሽ መስሎሽ ጠቃሚ
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out