Στίχοι

አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ ያ'ባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠንበለል ያ'ባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠንበለል ዋጥ ላርጋትና አላየሁም ልበል ዋጥ ላርጋትና አላየሁም ልበል እኔ አይኔን አሞኛል ወይ አልሞት አልድን እኔ አይኔን አሞኛል ወይ አልሞት አልድን እሷንም ጥሎባት እንደኔ ትሁን እሷንም ጥሎባት እንደኔ ትሁን አይሽ አይሽ እና ሳቅ ይከጅለኛል አይሽ አይሽ እና ሳቅ ይከጅለኛል እኔ ያሳለፍኩት ባንቺ ይታየኛል እኔ ያሳለፍኩት ባንቺ ይታየኛል አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ ባይንሽ ጉድፍ ገባ ሁሉን አይ ብለሽ ባይንሽ ጉድፍ ገባ ሁሉን አይ ብለሽ ሳያምሽ አይቀርም ሳይቆረቁርሽ ሳያምሽ አይቀርም ሳይቆረቁርሽ ምነው ኩላሊቴን ምነው የደሜን ስር ምነው ኩላሊቴን ምነው የደሜን ስር የዋለ ያደረ ጥል ያለን ይመስል የዋለ ያደረ ጥል ያለን ይመስል ባዛኚቱ ማርያም በወለላይቱ ባዛኚቱ ማርያም በወለላይቱ የታመመ ሳይድን አይንጋ ሌሊቱ የታመመ ሳይድን አይንጋ ሌሊቱ አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ እስኪ ሰው ጥሩልኝ እኔ ድምፅ የለኝም እስኪ ሰው ጥሩልኝ እኔ ድምፅ የለኝም ርቆ ከሄደ ወዳጅ አይገኝም ርቆ ከሄደ ወዳጅ አይገኝም ትላንትም አልበላሁ ዛሬም ፆሜን አደርኩ ትላንትም አልበላሁ ዛሬም ፆሜን አደርኩ ሰውም አልጠየቀኝ እኔም አልተናገርኩ ሰውም አልጠየቀኝ እኔም አልተናገርኩ ቁና ጥሬ ልብላ አመት ልመንን ቁና ጥሬ ልብላ አመት ልመንን እሷን በሱባዬ አገኝ እንደሆን እሷን በሱባዬ አገኝ እንደሆን እኔ ቤቷ አልሄድም እሷን እፈራለው እኔ ቤቷ አልሄድም እሷን እፈራለው አይኗ ሰው ይዋጋል ሲሉ ሰምቻለው አይኗ ሰው ይዋጋል ሲሉ ሰምቻለው አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወድጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
Writer(s): Traditional Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out