Lyrics

መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን ተሻለው ከሩቅ ሳትስቢ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንቺ በላይ ዕዉቀታቸው ስቄም ነበር በቀልዳቸው ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን ተሻለው ከሩቅ ሳትስቢ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንቺ በላይ ዕዉቀታቸው ስቄም ነበር በቀልዳቸው ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ለኔው ጥቅም በኔው ሰው ተመክሬ አላውቅም አድምጬ ከልብ አምርሬ አሁን ለምን ገባኝ ባንቺ ስመከር ያሉኝን ብለሺኝ የምፍጨረጨር ከኔ ነው ወይ ካንቺ ነው ልቤን ለእጅሽ የሰጠነዉ ማኩረፍ የኔ ነበር አልሸፋፈንኩም ካንቺ ጀምሬ ግን አልተቀየምኩም ምንድነው ብርቅ ሆኖ የሚያስወድደኝ ሁሉሽን እንዳደንቅ የሚያስገድደኝ የት ብለው የት ቢሄዱ መስፈርት የለም ከወደዱ መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን ተሻለው ከሩቅ ሳትስቢ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንቺ በላይ ዕውቀታቸው ስቄም ነበር በቀልዳቸው ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ተቀይሯል ዓይኔ ወዷል መልክሽን ሲመስሉሽ ያደንቃል ሲቀርቡሽ አንቺን ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ ዓይነት ብቻ ባይም ልቤ አያምንም እንዳለሽ አቻ የት ብለው የት ቢሄዱ መስፈርት የለም ከወደዱ ተቀይሯል ዓይኔ ወዷል መልክሽን ሲመስሉሽ ያደንቃል ሲቀርቡሽ አንቺን ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ ዓይነት ብቻ ባይም ልቤ አያምንም እንዳለሽ አቻ ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
Writer(s): Samuel Alemu, Eyob Mekonen Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out