Music Video

Teddy Afro - Mar eske Tuwaf (Fikir Eske Meqabir)
Watch {trackName} music video by {artistName}

Credits

PERFORMING ARTISTS
Teddy Afro
Teddy Afro
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Teddy Afro
Teddy Afro
Songwriter

Lyrics

የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል ተሸፈና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም ፍቅር የበዛበት ዘልቆ ከማንኩሳ መንናለች አሉኝ ቢጫ ልብስ ለብሳ ሸዋ ከሩፋኤል ስጠብቃት ኖሬ ንቤ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ ሲኖዳ ዮሐንስ ያመት ወዜን ይዤ ጋማ ሽጦ ካሳ ሸኝቶኝ ከወንዜ መጥቼ ከሸዋ ስጠብቃት ኖሬ ለካ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ "ሀ" ብለህ ተው ድገም ሲሉኝ ንስሀ አባቴ "ዋ" ብየ ተማርኩኝ አይ አለመስማቴ ቀለም ወርቄ ቢሆን የቅርቤ ጓደኛ ፍቅር ለያዘው ሰው ከልካይ የለው ዳኛ አሁን በማ ትኬ (ተክቼ) ይህ ልቤን ልካሰው አንዴ በሷ ፍቅር የተረታሁኝ ሰው የት እርቄስ ላገኝ ከፍቅሯ መሸሻ እሷ ሆና ለኔ የአለም መጨረሻ ማር ጧፍ ሁኔ ማር ጧፍ ሁና ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ (ኦሆ) ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ ያቺ ወንጌል ቢጫ ለብሳ ከንግዲህማ ቆብ አስጥዬ እንዳልወስዳት አባብዬ ሰብልዬ ናት እማሆዬ ሰብልዬ ናት እማሆዬ ሰብል አለም በቢጫው ቀለም ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም (ኦሆ) የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል ተሸፍና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም ላሳደገኝ ደብር የሥለት ልጅ ሆኜ ካሕን እንዴት ይፍታኝ ያንቺ እስረኛ ሆኜ በጊዜ ተደፋ የቀለሙ ቀንዴ የኔ ፊደል ማወቅ ካንቺ አዳነኝ እንዴ ሳዋህድ ከኖርኩት ቅኔን ከደብተሬ ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ ለካ ሰው አይድንም በደገመው መጽሐፍ እንደሰም አቅልጦ ፍቅር ካረገው ጧፍ ለካ ሰው አይድንም በኦሪቱ ገድል ወንጌል ይዞ መጥቶ ፍቅር ካረገ ድል ማር ሲገባ ገዳም ድንጋይ ተንተርሶ ጧፉም እንደ መናኝ እዩት ቢጫ ለብሶ ወንጌል መነኮሱ በልጅነታቸው ማር እስከጧፍ ሆኖ አለም ቢነዳቸው አንቺ የፍቅር ጥጌ ውድነሽ በጣሙን መምጣቴ ነው በቃ እኔ አቃተኝ አሁን አዲስ አለም ሆነ ባንቺ ስል ወጋየሁ እድሌ ሆነና ባጣሽ ተሰቃየው ማር ጧፍ ሁኔ ማር ጧፍ ሁና ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ (ኦሆ) ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ ያቺ ወንጌል ቢጫ ለብሳ ከንግዲህማ ቆብ አስጥዬ እንዳልወስዳት አባብዬ ሰብልዬ ናት እማሆዬ ሰብልዬ ናት እማሆዬ ሰብል አለም በቢጫው ቀለም ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም (ኦሆ) ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ ዘንግ ይዛ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out