Lyrics

ተንገበገበልሽ አረረልሽ ሆዴ አትራቂኝ በኔ ሞት አይብዛ መንደዴ ያስታርቀን መውደዴ ልመናዬን ስሚ ይቅርታሽ ይድረሰኝ ጥፋቴን ለመርሳት እኔ አቅም አነሰኝ ልቤ እየወቀሰኝ ከትዝታሽ ንዳድ አልዳነም አንጀቴ አንቺን ካጣሁ ወዲህ ተጨንቋል ስሜቴ አልበላም አልጠጣም እምቢ እያለኝ ሆዴ በይግባኝ ሳይታይ ሊቀር ነው ወይ ፍርዴ የእድሜን ጠዋት ማታ በትካዜ ገፋው አጣሁት ሰላሜን አንቺን ስላስከፋው ያለውን ችያለው መጪው ካልከበደኝ ጸልይልኝ ፍቅርሽ እንዳያሳብደኝ ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ እወዳታለው ማለት አይሰለቸኝ እወዳታለው ማለት አይሰለቸኝ ተራዬን ብነሳ ልበር እንደ ግዴ ብመርጠው መራቁን አይቀናኝ መንገዴ ስቴጂ ቢከፋኝ ስሞታ አላሰማ ተለየሽኝ ብዬ ዛሬ አንቺን አላማ ክፉሽን አውርቼ አልኖርም ሲቆጨኝ ቅናት ነው ጠላቴ የሚያነጫንጨኝ ዳርእስከዳር ብዞር ልክሽን አላገኝ ልርሳሽ ብል መንፈሴ ሰውም አያረገኝ እምባዬን ባፈሰው አፍ ላይደቅንበት የኔ ቃላት ናቸው ፍቅሬን የቀኑበት አይኔን እየረሳሁ በዛፍ በቅጠሉ ተብሰልሳይ አርጎኛል ካንቺ መነጠሉ ትካዜን አጥምደው ምንም ቢፈዙበት ያዩበታል እንጂ ወፍን አይዙበት እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ አንድም ጸጽቶኛል ለሱም በይኝ ይቅር አይለመደውም ቅጣት ሰው ሲቀጣው ፍቅር ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ አንድም ጸጽቶኛል ለሱም በይኝ ይቅር አይለመደውም ቅጣት ሰው ሲቀጣው ፍቅር ኧ.ሀ... ሀ.ሀ... ኧ.ሀ.ሀ.ሀ ምነው በትዝታ ሁሌ እንደምመኝሽ ከጉጉቴ መረብ ተቀምጠሸ ባገኝሽ እኔ አዳኝ አይደለሁ አላልም በጫካ ምንሽሬ እምባ ነው ህልሜም ባይሳካ ብዙ ማልቀስ ባዳም ባይለመድ እንኳን ባንቺ ሀዘን ልቤ ላይ አስጥያለው ድንኳን ብትባበርኝም ምድር ለአራት ታጥፋ አብረን እንኑር እና እስኪ አምኜሽ ልጥፋ ቀራንዮም ይስማ ጎሎጎታም ይወቅ አይረዳን ምህረቱ እኛ ሳንታረቅ ባይጻፍም ሰአት ለአለም መጨረሻ ቀን ማጣት ምጻት ነው አንቺ መመለሻ እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ
Writer(s): Simone Tsegay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out