Lyrics

ነገን ለትዝታ አዲስ ስጦታ ለእኔ የሚሆን ሳታውቅ ሰምታ እንደ ነብይ ቃል አብሮ እንደሚኖረው ተከብሮ በሀገሩ እልፍ እንደሚያልፈው እውነት ዛሬ ይንገስ ነገን ስለሚያውቅ እውነት ዛሬ ይንገስ ነገን ስለሚያውቅ አባቴ እናቴን ባያገኝ እኔ አልኖርም ነበር አያቴም እሷን ባያገኝ እሱ አይኖርም ነበር ፊቱንም እኔ ላድንቀው የማልም የነገን እኔም ዛሬን ባላገኝ ነገ ላይኖር ነበር ኋላው ጥላ ሆኖ ታሪክ አላመልጠው ነገር ነገን ብቻ እያየው ልሮጥ ስንደረደር አዋቂ ስሆን ልጅ ሳድግ ደግሞ አዋቂ ትምህርት ከዛሬ አዎ እንደቀን ጠባቂ የዕለት የዕለት እውቀት ቢገኝ እንደው ለነጠላ ሀምሳ ሎሚ ከባድ ነው ከሆኑ ለብቻ እንደሚታደል ነግሬ የእኔን ወሰድኩ ዛሬ የድርሻውን ወስዶ ሁሉም ታደለች ሀገሬ የእኔን የዛሬ ደግሞ ለእነሱ የነገ ከአካፈሉኝ ከትናንት ለእኔም ዛሬ ሆነ በነበር አልቀረም ድሮ አልቀረም ለዛሬ ሰው ሆኗል ዛሬም አማረበት በቃ ታግዞ በትናንት በል ያም ያውራ ለእሱ እሱም ያውራ ለእሷ እሷም ብትናገር ምንም ሳትጨምር የሰማውም ሰምቶ ላልሰማው ቢነግር ቢያረገው ቀና ቢሆን ቁምነገር ቢናገር ነው ሰው ሁሉም ይማከር ቢናገር ነው ሰው ሁሉም ይማከር ቢናገር ነው ሰው ሁሉም ይማከር በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ ሲነገር ይነገር ይነገር ሰላም ያለው ነገር በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ ሲነገር ይነገር ይነገር ሰላም ያለው ነገር እኔ ደግሞ ስናገር ከሀገሬ ሰው ጋር ስማከር ሀሳቤን ሁሉ ሰብስቤ ሰላምታዬንም አቅርቤ አንደበት ባለው ውብ ለዛ በክፉ ነገ እንዳልወሳ ግርማ ሞገሱን ከአንበሳ ተኝቶ ውሎ ሲነሳ ሳይጠየቅ ጥያቄ የሚያሳብ ለምላሹ የማይቆጥር ውለታ እንዳይቆጥሩት እነሱ ልጅ ሆኖ ሳለ ራሱ ምኞቱ ለታናሹ ቸልተኛ ቅፅሉ በቅንፍም ታጋሹ ...ስር ንቅሳት በእራሷ ቀለም ላድሳት ያለሁት እዚው ከተማ በውቧ በአዲስ አበባ የሀገር ሰው ይሄን ሲሰማ ድሮን ብሎ ቢለማ ነገንም ደሞ ሲያልመው አንድላይ ብንሆን ቢያስበው ድሮም ድሮም ተዋግተው አሁን ደሞ ተዋደው ያኔም ለአንድ አላማ አሁንም ይኸው አላማ ፍቅር ፍቅር ተሞተ ፍቅር ፍቅር ይሰማ ፍቅር ፍቅር ተሞተ ፍቅር ፍቅር ይሰማ በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (አምሮብን አዎ እንታይ) ሲነገር ይነገር ይነገር (አምሮብን አዎ እንታይ) ሰላም ያለው ነገር በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (አምሮብን አዎ እንታይ) ሲነገር ይነገር ይነገር (አምሮብን አዎ እንታይ) ሰላም ያለው ነገር በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (ፍቅር ፍቅር ተሞተ) ሲገር ይነገር ይነገር (ፍቅር ፍቅር ይሰማ) ሰላም ያለው ነገር በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (ፍቅር ፍቅር) ሲነገር (ፍቅር ፍቅር) ይነገር ይነገር ሰላም ያለው ነገር
Writer(s): Fikru Sema Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out