album cover
Naet
6,382
World
Naet was released on June 22, 2022 by Teddy Afro as a part of the album Naet - Single
album cover
Release DateJune 22, 2022
LabelTeddy Afro
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM149

Credits

PERFORMING ARTISTS
Teddy Afro
Teddy Afro
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Tewodros Kassahun
Tewodros Kassahun
Songwriter

Lyrics

ዶፍ!
ዶፍ!
ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)፣ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)፣ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)
ማን ሊታደም ከድግሱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)፣ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)
ብልጭልጭ ቢሆን ድንኳን
ኡኡ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)፣ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)
አይለውጥ ጎግ የእውነት መልኳን
ቢጋርድ ሃሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ኡኡ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)፣ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)፣ ሬጌ ናዕት (ሬጌ ናዕት)
ማን ሊታደም ከድግሱ
ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ
ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት
(እያመመው መጣ) እያመመው
(እያመመው መጣ) እያመመው መጣ
(እያመመው መጣ)
ያዳፈነው እሳት (እያመመው መጣ)
ከሆዱ ሳይወጣ (እያመመው መጣ)
ልቤ እንደካቻምናው (እያመመው መጣ)
እያመመው መጣ (እያመመው መጣ)
የሚያዜም ይመስላል (እያመመው መጣ)
ሲያጣጥር ተጨንቆ (እያመመው መጣ)
ውስጡን ሲሰብቅለት (እያመመው መጣ)
ኡ! እያለ ማሲንቆ (እያመመው መጣ)
(እያመመው መጣ) እያመመው መጣ
(እያመመው መጣ) እያመመው መጣ
(እያመመው መጣ)
የተረገጠ እውነት (እያመመው መጣ)
በጊዜ ውስጥ እግር (እያመመው መጣ)
ታፍኖ የቆየ (እያመመው መጣ)
በሆታ ግርግር (እያመመው መጣ)
ትንሽ ጋብ እንዳለ (እያመመው መጣ)
የጭብጨባው ጩኸት (እያመመው መጣ)
እረጭ ሲል ውሸት (እያመመው መጣ)
ይናገራል እውነት (እያመመው መጣ)
እያመመው መጣ (እያመመው መጣ)
እያመመው መጣ (እያመመው መጣ)
ቂምን ሻረውና (እያመመው መጣ)
ወይ ፍቅርን አንግሠው (እያመመው መጣ)
ሁለት ሆኖ አያውቅም (እያመመው መጣ)
አንድ ነው አንድ ሰው (እያመመው መጣ)
ከሀገርም ይሰፋል (እያመመው መጣ)
ያ የፍቅር ገዳም (እያመመው መጣ)
መጠሪያው ሰው እንጂ (እያመመው መጣ)
ዘር አይደለም አዳም (እያመመው መጣ)
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ!
ዳር አለው እንዴ ድንበር (ዳር አለው እንዴ)
ዳር አለው እንዴ ፍቅር (ዳር አለው እንዴ)
የዘር ሐይማኖት ድንበር (ዳር አለው እንዴ)
ዳር አለው እንዴ ፍቅር (ዳር አለው እንዴ)
በዚህ ለፀና እውነት (ዳር አለው እንዴ)
የፍቅር ሀገር ከጥንት (ዳር አለው እንዴ)
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከሞት (ዳር አለው እንዴ)
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት (ዳር አለው እንዴ)
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት (ሀገሬን)
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት (ሀገሬን)
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት (ሀገሬን)
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት (ሀገሬን)
ሀገሬን ላልረሳት (ሀገሬን)
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዶፍ! (ቃል አለኝ)
Written by: Tewodros Kassahun
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...