Credits

PERFORMING ARTISTS
Abel mulugeta
Abel mulugeta
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Abel mulugeta
Abel mulugeta
Songwriter

Lyrics

ያሉትን ይበሉ ፍቅሯ ከረታኝ
የወደደ ሟች ነው ይሄ መች ጠፋኝ
የልቤን ካገኘሁ ከተሳካልኝ
ለሚያልፍ አሉባልታ እኔስ ግድ የለኝ
ባልዋልኩበት ውዬ ስሜ እንኳ ቢጠፋ
ቃልኪዳን አለብኝ ፍቅርሽን ላልገፋ
ቢወራ ቢነገር በድፍን ከተማ
እኔስ ማንንም አልሰማ (ማንንም አልሰማ)
ከላይ ሳይታደል በይሆናል ብቻ
ሰው እንደፍቃዱ አያገኝም አቻ
ይህን መሳይ ፍቅር ለኔ ካለውማ
እኔስ ማንንም አልሰማ (ማንንም አልሰማ)
ከዘሯ አይደለም ጉዳዬ
መታመን ብቻ ነው እዳዬ
ከገባው ፍቅር ስሙ
አይኮራም በዘር በደሙ
ከየት ትሁን ከየት ግድ የለኝም
የሷ ዘር ፍቅር አይሆነኝም
ካማረኝ እሷን ካልኩማ
አልሻም ምክርም አልሰማ
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
ያሉትን ይበሉ ፍቅሯ ከረታኝ
የወደደ ሟች ነው ይሄ መች ጠፋኝ
የልቤን ካገኘሁ ከተሳካልኝ
ለሚያልፍ አሉባልታ እኔስ ግድ የለኝ
ከምእራብ ከደቡብ ከሰሜን ምስራቅ
በዘር መሞሻሸር እኔ እንደው አላውቅ
ካልተጠራጠራት ልቤ ካመነማ
እኔስ ማንንም አልሰማ (ማንንም አልሰማ)
ልጅ አድጎ ይለያል ከ'ናቱ ካ'ባቱ
ሊጣምመር በፍቅር ከወደዳት ሚስቱ
ደምሮ ቀንሶ ሀቁን ካገኘማ
ልቤስ ማንንም አይሰማ (ማንንም አልሰማ)
ከዘሯ አይደለም ጉዳዬ
መታመን ብቻ ነው እዳዬ
ከገባው ፍቅር ስሙ
አይኮራም በዘር በደሙ
ከየት ትሁን ከየት ግድ የለኝም
የሷ ዘር ፍቅር አይሆነኝም
ካማረኝ እሷን ካልኩማ
አልሻም ምክርም አልሰማ
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
አልሰማም አልሰማም
Written by: Abel mulugeta
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...