Lyrics

ጭር አለ አንቺን ያጣው ደጄ እምባ ነው ከእንግዲህ ወዳጄ እኔማ ሳላይሽ ከርሜ እህ እላለው በናፍቆት ታምሜ ሊመሽ ነው አድማሱ ጠቆረ የልቤ ትርታ ጨመረ እእ እህ ይከፋኝ ጀመረ ሊመሽ ነው አድማሱ ጠቆረ የልቤ ትርታው ጨመረ እእ እህ ይከፋኝ ጀመረ የኔ ጎጆ የኔ ታዛ ፅልመት የወረሰው ይቺን አለም እንዴት ልግፋት ብቻዬን ያለ ሰው ባዶ ቤቴን ዘጋግቼ ከማንባት በቀር ምን ምርጫ አለኝ ተፈርዶብኝ ያ'ላንቺ እንድኖር ከአይኔ እምባ ሲቀዳ እየዋለ አለሁኝ መኖር ከተባለ እእ እህ ቅስሜ እንክት እንዳለ ጥንድ ሆነው ያየው እለት በአይኔ ይበዛል ይከብዳል ሀዘኔ እእ እህ እንዴት ልሁን እኔ ጭር አለ አንቺን ያጣው ደጄ እምባ ነው ከእንግዲህ ወዳ እኔማ ሳላይሽ ከርሜ እህ እላለው በናፍቆት ታምሜ በመውደድ አልሰራው በደል ከረምኩኝ በሀሳብ ስዋልል እእ እህ አለመታደል መለየትሽን አምኖ ልቤ መቀበል ተሳነው ጓዳ እልፍኙ መኝታውም አንቺን አስታዋሽ ነው በትዝታሽ እጽናናለሁ በቀሪው ዘመኔ በቃ እርሜ ነው ከአንቺ ሌላ አላፈቅርም እኔ በናፍቆት እየተፈተንኩኝ ተጎዳሁ ለፍቅርሽ ባዘንኩኝ እእ እህ ዛሬስ ተሸነፍኩኝ እንኳንስ እኔ ባለቤቱ ናፍቆትሽ የጎዳኝ በብርቱ እእ እህ ተርቦሻል ቤቱ መች ይሆን አይንሽን አይቼ በሰላም የማድረው ተኝቼ እእ እህ መብሰልሰሌን ትቼ እእ እህ መብሰልሰሌን ትቼ
Writer(s): Meselle Getahun Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out