Lyrics

እትቱ እትቱ በረደኝ እትቱ በቀን በፀሐይ እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱን እትቱ ይዞት ገባ ወይ ዛሬስ ዛሬስ ከዓይኔ ባጣሽ ዛሬስ ድንገት በማርፈድሽ ዛሬስ ላምባዬን አንስቼ ወጣሁኝ ወጣሁ ልፈልግሽ ዛሬስ ወጣሁ ልፈልግሽ እትቱ እትቱ በረደኝ እትቱ በቀን በፀሐይ እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱን እትቱ ይዞት ገባ ወይ ዛሬስ ስፍስፍ አልኩኝ ባንቺ ዛሬስ ሰውነቴም ከዳኝ ዛሬስ በልቤ አለ ነገር በሰው በሰው አፍ ላይዳኝ ዛሬስ በሰው አፍ ላይዳኝ በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩ እንደ ጅል እኔስ ባንቺ ጉዳይ ብልጠትን አልከጅል ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ ዓይኔ አንቺን ካላገኘው መንጋቱስ ለምኔ ዋ! የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ ውሃውን አስረሳኝ ሲፈስ ወደ አንጀቴ ወንዙ ዳር አጥምቂኝ መልክሽ ይታየኛል አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል በወግ ያልነኩትን ዘራፍ ሲሉት ሸሽቶ ይታገለኝ ጀመር ፍቅርሽ ጦር አንስቶ አንቺው ምከሪልኝ ዘንጉን ይመልሰው ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው አቤት አቤት አቤት አሃሃ አቤት አቤት አቤት ሃ... ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ...
Writer(s): Abebe Birhane, Natnael Getachew Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out