Lyrics

ጥሮ አዳሪ ለፍቶ አዳሪ የእግዜር ደሀ ደክሞ ኗሪ ደግ እሩሩህ ልበ ቀና በሰው ኑሮ የማትቀና እንደልፋቷስ ማን በለጣት እድሏ ነው የሚያስቀጣት ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት ምስኪን ደሀ ናት ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት ደክሞ ኗሪ ናት አስተዋይ እና አርቆ አሳቢ ዘመድ አዝማድን ሰብሳቢ አስተማሪ ሁሉን አዋቂ መካሪ ናት አስታራቂ አዛኝ ሰው ናት የምትሳሳ ክፉ ደጉን የማትረሳ ደሀ የኔ ደሀ ደሀ የኔ ደሀ ከርታታ ጨዋ ተዋት ለኔው ተዋት ተዋት እሷን ተዋት ደክሞ ኗሪ ናት ተርፎ ባይተርፋትም አውቃለው ደሀ ናት አታንስም ለራሷ የጤናም ሀብታም ናት ሁሉን መስሎ ኗሪ ፀባይዋ ጉልበቷ ደስታዋ ስራ ነው ጎጆዋ ኩራቷ አሀሀ የማትገዛ አሀሀ ለብልጭልጩ አሀሀ የድሀ ጎበዝ አሀሀ የኩራት ምንጩ አሀሀ የማትደለል አሀሀ ባልረባ ነገር አሀሀ እጇን የማትሰጥ አሀሀ የማትበግር የኔ ጎበዝ የኔ ደሀ ፍቅሯ 'ማይደርቅ የምንጭ ውሀ ሀብታም በብር ቢያቅናጣም ደሀ እንዳቅሙ ፍቅር አያጣም ጥረው ግረው ያገኙት ይጣፍጣል ሲበሉት ቆሎም ሽሮም ጮማ ናቸው ሰው ተፋቅሮ ከበላቸው አቻም የለሽ ሰው ይላታል ለመጠርያ ስም ያንሳታል ቢደላትም ባይደላትም የሚያውቅላት ሰው የላትም እዘኑላት እባካችሁ ደሀ አክባሪ የሆናችሁ ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት ደክሞ አዳሪ ናት ተዋት እሷን ተዋት ተዋት እሷን ተዋት ለፍቶ ኗሪ ናት ላንድ እራሷ አንሳ አታውቅም ትደክማለች እረፍት የላትም ካላት ከፍላ ኑ ጉረሱ የምትል ናት ተቃመሱ ሀብቷ ጌጧ ድህነቷ ፈጣሪዋ ነው ጉልበቷ ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት ደክሞ አዳሪ ናት ደሀ የኔ ደሀ ደሀ የኔ ደሀ ከርታታ ጨዋ ስጦታዋ እውነት በረከቷ ምክር አምኖ ለተጠጋት ፍቅር የምታበድር ከሷ ጋራ ኑሮ ለኔ ተስማምቶኛል ጠግቤ ባላድርም ሰላሜ ተርፎኛል አሀሀ የማትገዛ አሀሀ ለብልጭልጩ አሀሀ የድሀ ጎበዝ አሀሀ የኩራት ምንጩ አሀሀ የማትደለል አሀሀ ባልረባ ነገር አሀሀ እጇን የማትስጥ አሀሀ የማትበግር የኔ ጎበዝ የኔ ደሀ ፍቅሯ 'ማይደርቅ የምንጭ ውሀ ሀብታም በብር ቢያቅናጣም ደሀ እንዳቅሙ ፍቅር አያጣም ጥረው ግረው ያገኙት ይጣፍጣል ሲበሉት ቆሎም ሽሮም ጮማ ናቸው ሰው ተፋቅሮ ከበላቸው አይ አይ ኡሁሁሁ አቤት አቤት
Writer(s): Neway Debebe Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out