Music Video

5. Bereket Tesfaye ማራናታ Maranata በረከት ተስፋዬ
Watch {trackName} music video by {artistName}

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Bereket Tesfaye
Bereket Tesfaye
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Bereket Tesfaye
Bereket Tesfaye
Songwriter

Lyrics

የመምጣትህ ነገር የመጨረሻው የነገርከን ትንቢት እየሆነ ነው ናፍቆቱ አስባለንኝ አሜን ማራናታ ላይህ ጓጉቻለው ኢየሱስ የኔ ጌታ ጌታ ኢየሱስ አትመጣም ወይ የደማልኝን ጎንህን ልይ አንተን ለማየት አይኖቼ ሻቱ ቶሎ ናልኝ ኢየሱስ የናዝሬቱ ካንተ ጋር ልዋል ካንተ ጋል ልደር እንደ ዮሕንስ በደረትህ ስር ደስታዬ የምለው ትልቁ እርካታዬ አንተ ያለህበት ስኖር ነው ጌታዬ በሌለህበት ከማገኝ ድሎት ምድረበዳ ላይ ካንተ ጋር ልሰንብት አንተን የማየት ናፍቆት ገባብኝ እንደጓጓሁኝ መች አቀራለሁኝ ከአመጻ ብዛት ፍቅር ቀዘቀዘ ሰው ወንድሙን ገሎ መቼ ተወቀሰ አመጸኞች በዙ ክፋቱ ጨምሮ ተላልፈው ተሰጡ ለማይረባ ዐዕምሮ የድኆች ዳኛ የሁሉ አለቃ ናና ከልከለው ለቅሶአችን ይብቃ የናቶች እንባ ይላል ዋይ ዋይ ሩህሩህ ጌታ አትመጣም ወይ ቤተ ክርስቲያን ተነሺና አብሪ ፍቅርን ለጣሉ እንዳዘምሪ የገሃነም ደጅ ለካ ጥላቻ ነው ማይቋቋምሽ ሰይፍሽ ፍቅር ሲሆን ነው ጦር መሳሪያውን ፍቅር ያደረገ ጠላቱን ረቶ ወንድም አደረገ የሰው ጠባብ አፍ የሚጎርስ እህል ክፉ አንደበት አክሎአል ሲኦል አትመጣም ወይ (ማራናታ) አናርፍም ወይ (ማራናታ) አትመጣም ወይ (ማራናታ) አናርፍም ወይ (ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) ሃሳቢ መምህራን ነብያቶች በዙ ተናገረኝ ባዮች ለገንዘብ የተገዙ ለታመመው ምስኪን የእንግዳ ማረፊያ በሽታው ሳያንሰው በፀሎት ሰበብ ዝርፊያ ደምህ ተረግጦ ገንዘብ ገነነ አንተን ያወቀ ሰው ክፉ ሆነ ነዋይ ሚያፈቅር ትውልድ ተነሳ ያረግክለትን ምህረት የረሳ ፈውሱ ለታይታ ለንግድ ቀረበ በአዳኙ ስም ገንዘብ ተሰበሰበ ገበያው ደርቶ በወንጌል ሰበብ ስንቱን ታዘብነው አወይ ጉድ አጀብ በሰጠው ጸጋ የሆነ ነጋዴ በፍርድ ቀን የሚል ነው ወይኔ ጉዴ መምጣቱ አይቀርም የእረኞች አለቃ ስለ በጎቹ የሚራራ ጠንቃቃ አትመጣም ወይ (ማራናታ) አናርፍም ወይ (ማራናታ) አትመጣም ወይ (ማራናታ) አናርፍም ወይ (ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) ወደ ዐለም ሂዱ ወንጌልን ሰብኩ ነበር የተባልነው መስክሩ ታደጉ ሰው ግን ካስማ ሰርቶ ወንበሯን ወደደ መምህር እና ጌታ መባልን ለመደ ወንጌል እንስራ አንቱታው ቀርቶ ይሽለም የል ወይ የሰራ ተግቶ ከታበይንበት ዙፋናችን እስኪ እንውረድ ለጌታችን አላወጣንም አጋንንቶችን? አልፈወስንም ወይ በሽተኞችን? ጌታ በስምህ ብዙ አድርገን አላውቃችሁም ስለምን አልከን? ከሚሉት ወገን እንዳይሆን ህይወቴ መብራቴን ላብራ ሳይጎድል ዘይቴ እስከምትመጣ ወይ እስክትወስደኝ እየጠበኩኝ እጸናለሁኝ (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ) (ና ና ና ና ና ማራናታ)
Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out