album cover
Gubeleye
album cover
Gubeleye was released on February 9, 2024 by ela records as a part of the album Enzira
AlbumEnzira
February 9, 2024
Labelela records
BPM120
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Lyrics

ያለ ነበር በዚህ መደሰት መከፋት
የሚኖር ነው ነገም ካሉ መውደቅ መነሳት
አንድም ሰው ለማግኘት አንድም ሰው ለማጣት
ለማጣት
መንገድ አይደለም ወይ የመሄድ የመምጣት
የመምጣት
ስለይሽ የኔ ሰው ያልኩሽን ከጎኔ
በጊዜው መንገድሽ ሳይገባኝ ኖሬያለሁኝ እኔ
የኖሩት ሲያልፍ ይሆን የለም ወይ ትዝታ
ነገሩን እስኪ እናንሳው ዛሬ እንዲያው ለጨዋታ
አጋርሽ መሆኑን ሰምቼ
ያ የጥንት ወዳጅሽ ወዳጄ
እቴ ሙች ግራ ነው የገባኝ
ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ ባይ
እስኪ ግለጪልኝ ይሄን ነገር ይሄን ነገር
ያ ሰው የዚያን ጊዜ ምንሽ ነበር ምንሽ ነበር
ኧረ እየው ድማሙ
ኧረ እየው ድማሙ
አሁን ምን ይሉታል ይህ አይነት ጨዋታ
ትተኸው የለም ወይ አንተው ያንተን ፋንታ
(ጉብልዬ) አንተ ጉብልዬ
(ጉብልዬ) አንተ ጉብልዬ
(ጉብልዬ) አይተኸው በሌላ
(ጉብልዬ) ባይገባህ ነው እንጂ
(ጉብልዬ) እርቅ አላሚ ነበር የአንተማ ወዳጅ
(ጉብልዬ) ወጉማ አጎንብሶ
(ጉብልዬ) ለምስጋና ነበር
አናከሰው ስንቱን አወይ የሰው ነገር
(ጉብልዬ) ጥለው ባያነሱም
(ጉብልዬ) የተዉትን ነገር
(ጉብልዬ) ዞረው ባያዩትም
(ጉብልዬ) የራቁትን ሀገር
(ጉብልዬ) እውነታ ቢሆንም
(ጉብልዬ) ዛሬን መስሎ ማደር
(ጉብልዬ) አይከፋም አንዳንዴ
(ጉብልዬ) ትላንትን መጠርጠር
(ጉብልዬ) አብረሽኝ እያለሽ
(ጉብልዬ) የነበረው ባዳ
(ጉብልዬ) መች ይሆን ተዛምዶሽ
(ጉብልዬ) ያረገኝ እንግዳ
ትላንት እንግዳዬ የነበረው ጎብኚ
ትላንት እንግዳዬ የነበረው ጎብኚ
ይኸው ዛሬ ደሞ እኔ እንግዳው ነኝ አሂሂሂሂ
ኧረ እየው ድማሙ
ኧረ እየው ድማሙ
ኧረ እየው ድማሙ
ኧረ እንደው ድማሙ
እንዴት ባልዋለበት ሰው ይጠፋል ስሙ አሄሄ
እንደተድላው ጊዜ እንደደስታው ቀን
እንደተድላው ጊዜ እንደደስታው ቀን
ሰው ከሰው ይውላል መቼም በሃዘን አሄሄ
አባባይ ሆንኩ እንጂ ላጎደልከው ደስታ
አባባይ ሆንኩ እንጂ ላጎደልከው ደስታ
እኔስ አልመኝም የወዳጄን ቦታ አሄሄሄ
አለምዬ
አለምዬ አለም ሸጋ ቁጭ ብለን እናውጋ
አለምዬ አለም ሸጋ ቁጭ ብለን እናውጋ አሄሄ
Written by: Mastewal Eyayu, Natnael Girmachew
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...