Lyrics

ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለሁ ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ እተክዛለሁ ውብ ጨዋታና ሳቅሽን አስታውሼ እህ እላለሁ እተክዛለሁ አስባለሁ አስባለሁ እንግዲያው አንቺም ከተለየሽ ከራቅሺኝ አስታውሺኝ በፍቅር ከደበቅነው አንጀት ከሆድሽ ውስጥ አታውጪኝ እንዳልረሳውሽ አደራ አንቺም አትርሺኝ አስታውሺኝ ፍቅሬ አስቢኝ አስቢኝ አስታውሺኝ እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ እንደምነሽ እንደምነሽ ከተሰናበትሽኝ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ እጠብቅሻለሁ መች ትመለሻለሽ ለብቸኝነቴ ለብቸኝነቴ ላዲሱ እንግዳዬ ትካዜ ብቻ ነው መስተናገጃዬ እንደምነሽ ብዬ ሁሌ አስብሻለሁ በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለሁ በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለሁ የኔ ፍቅር በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለሁ አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ ሲነጋ አሰብኩሽ አልዋሽም እኔ አልዋሽም የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለሁ ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ እተክዛለሁ ውብ ጨዋታና ሳቅሽን አስታውሼ እህ እላለሁ እተክዛለሁ አስባለሁ አስባለሁ እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ ከተሰናበትሽኝ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ እጠብቅሻለሁ መች ትመለሻለሽ ናፍቆትሽ በዓይኔ ላይ ናፍቆትሽ በዓይኔ ላይ ከተመላለሰ የፍቅር እመቤቴን አንቺን ካስታወሰ እንደምነሽ ብዬ አስታውስሻለሁ ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለሁ ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለሁ የኔ ፍቅር ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለሁ አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ ሲነጋ አሰብኩሽ አልዋሽም እኔ አልዋሽም የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም አልዋሽም እኔ አልዋሽም የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም አልዋሽም አልዋሽም የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
Writer(s): Neway Debebe Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out