Lyrics
ምን ተክቼ ልርሳ መውደዴን በምኔ
ሰው በሰው መተኪያ አላገኘም ጎኔ
ኃያል ፅኑ ፍቅርሽ ጀግኖ አይሏል
ቅስምንም ሰባብሮ ናፍቆትሽ ሰው ጥሏል
ኃያል ፅኑ ፍቅርሽ ጀግኖ አይሏል
ቅስምንም ሰባብሮ ናፍቆትሽ ሰው ጥሏል
ተጫዋችነት ፈገግታዬ ጠፍቶ
ባይተዋርነት ትካዜ በዝቶ
ልቤን ከፍቅሬ ጋር እኔው ልኬልሽ
ትዝታን አማጥኩልሽ
ተጫዋችነት ፈገግታዬ ጠፍቶ
ባይተዋርነት ትካዜ በዝቶ
ልቤን ከፍቅሬ ጋር እኔው ልኬልሽ
ትዝታን አማጥኩልሽ
ልረሳሽ አልቻልኩም ፍቅርሽ እረትቶኛል
ልለይሽ አልፈቅድም ኪዳን ሸብቦኛል
ምንድነው መፍትሄው መላው ብልሀቱ
መላ ካንቺ ካለ መላ በይኝ እቱ
ምንድነው መፍትሄው መላው ብልሀቱ
መላ ካንቺ ካለ መላ በይኝ እቱ
ሰበብ ሆነ ምክንያት ጊዜ ቦታ አይመርጥ
ፍቅርሽ ሲያብከነክን ውበትሽ ሲገለጥ
ትዝታሽ ነካክቶ ፍቅሬ ተቀስቅሶ
መብሰክሰክ መንደዴን ባየልኝ ደርሶ
ትዝታሽ ነካክቶ ፍቅሬ ተቀስቅሶ
መብሰክሰክ መንደዴን ባየልኝ ደርሶ
ተጫዋችነት ፈገግታዬ ጠፍቶ
ባይተዋርነት ትካዜ በዝቶ
ከጎኔ መራቅሽን
ልቤ እያወቀ ለምን ተጨነቀ
ተጫዋችነት ኦ ፈገግታዬ ጠፍቶ
ባይተዋርነት ትካዜ በዝቶ
ከጎኔ መራቅሽን
ልቤ እያወቀ ለምን ተጨነቀ
ልረሳሽ አልቻልኩም ፍቅርሽ እረትቶኛል
ልለይሽ አልፈቅድም ኪዳን ሸብቦኛል
ምንድነው መፍትሄው መላው ብልሀቱ
መላ ካንቺ ካለ መላ በይኝ እቱ
ምንድነው መፍትሄው መላው ብልሀቱ
መላ ካንቺ ካለ መላ በይኝ እቱ
ኦሆ ኦሆ አሀ
አልረሳሽ አልክድሽ
ከልቤ ላይ ተተክለሽ
አልችል አልኩኝ አንቺን መርሳት
ኦሆ ኦሆ
አልሆን አለኝ አንቺን መርሳት
ለኔ ሆነሽ የልብ እሳት
እንዴት ላቁም አንቺን መርሳት
Writer(s): Samuel Alemu, Danial Tamere Tekle
Lyrics powered by www.musixmatch.com