Lyrics

ሰባት 7 ፯ - አብዱ ኪያር ትላንት የማውቀውን ሁሉንም ቢያሳጣኝ ከፍቶኝ ተቀይሬ የሚያቀኝም ቢያጣኝ ፊቴ ተጨማዶ መልኬ ቢለወጥም ተደስቶ መሳቅ ጥርሴ ቢያቋርጥም ድህነትን በሞት መቸም አልለውጥም ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ ትላንት የነበረኝ ዛሬ ባይኖረኝም ወዳጆቼ ጠፍተው ፍቅሬ ብትርቀኝም አይኔ ጥሩ ነገር ቢተውም ማየቱን እጄም ለቅንነት ቢያቆም መዘርጋቱን መቸም አላቆምም ተመስገን ማለቱን ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out