Music Video
Credits
PERFORMING ARTISTS
Tekeste Getnet
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Tekeste Getnet
Songwriter
Lyrics
ጎንበስ ቀና ብለህ ያኔ በአምሳልህ የፈጠርከው
አልተገኘም በስፍራው ሆኖ አንተ እንዳስቀመጥከው
በምኞት ተሳበ ወደቀ በጠላት ተረታ
እራሱን በራሱ በደለ መቅሠፍትን አመጣ
የተፍገመገመ እንዳይወድቅ መድኃኒት ላክለት
እንደማይችል አውቀህ እንዲሁ ምህረት አድርግለት
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው
ፍጥረት ተቀሠፈ አለቀ እንዲሁ በከንቱ
እሮሮና ሃዘን ያሰማል ሁሉም በየቤቱ
ልጆች አዋቂዎች ሳይባል አዛውንቶች ሁሉ
ያለአጋዥ ያለጧሪ ቀርተው ጐዳናውን ሞሉ
ተንከራታቹን ሰው አስበው ልቡን መልስለት
ረሃብ ቸነፈር በሽታውን አንተ አስወግድለት
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተብከንክኗል በአምሳልህ የፈጠርከው
እረ ይቅር በለን ጩኸታችን ይውጣ
የሚያግዝ የለም ወይ እንዲህ ስንቀጣ
ወዴት አቤት እንበል ለማን እንንገረው
ፍጥረት ተቅበዝብዟል አጋዥ እንደሌለው
ከነገሥታት መፍትሄ ጠፍቷል
ከጠቢባን ጥበብ ተሰውሯል
አቅም ያለው ለውጥን የሚያመጣ
አንድም የለም ሚያድነን ከቁጣ
አንተ ግን ሁሉን ቻይ ነህና
የሚሳንህ ምንም የለምና
አግዘው እንጂ ተመልከተው
ይሄ ፍጥረት ያለአንተ ማን አለው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው
Writer(s): Tekeste Getnet
Lyrics powered by www.musixmatch.com