Music Video
Music Video
Credits
PERFORMING ARTISTS
Abdu Kiar
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Abdu Kiar Kahssay
Songwriter
Lyrics
መውደዴን ለመናገር ማፍቀሬን ለመናገር
ሳሰላስል ብዙ ሺህ ዓረፍተ ነገር
ባንድ ቃል ገደለችኝ ባንድ ቃል ገደለችኝ
የስሜትን ትርጉም አሳየችኝ
እወድሃለሁ ብላ በፍቅር ብትጠጋኝ
የምሆነው ነገር ነው የጠፋኝ
ግልፅነቷ ገደለኝ ኧረ ወየው ወየው
እንዲ ደምብሬ አላውቅም ሰውየው
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ባይኔ አይን አይኗን ወይኔ እኔ እያየሁ ወይኔ እኔ
ፍዝዝ አልኩኝ ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ቃል ሳይወጣኝ ወይኔ እኔ ዘገየሁ ወይኔ እኔ
ምን ልመልስ ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
አቤት ፍርሃት አቤት ፍርሃት
ንጹህ ፍቅሬን ላመታት ሳልነግራት
እየፈራሁ ስለቆየሁ
ዛሬ ቁጭት ልቤን አሰቃየው
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
እሷ ፍቅርን ተማምና እሷ ስሜቷን አምና
እኔ የፍቅር ጥቅሶችን ሳጠና
ላመታት ስሸመድድ ብራቀቅም በቃላት
ባንድ ቃል ነው ውሃ የሆንኩላት
እወድሃለሁ ብላ ስትጠባበቅ መልሴን
ልቤ መታ ፈነጠዘች ነፍሴ
ግልጽነቷን ድፍረቷን ከኔ ጋር ሳስተያየሁ
ድብቅም ነኝ ፈሪም ነኝ ሰውዬው
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ባይኔ አይን አይኗን ወይኔ እኔ እያየሁ ወይኔ እኔ
ፍዝዝ አልኩኝ ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ቃል ሳይወጣኝ ወይኔ እኔ ዘገየሁ ወይኔ እኔ
ምን ልመልስ ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ሳያንኳኩ አይከፈትም
ሳይጠይቁ ምንም መልስ አይሰጥም
ድብቅ ሆኜ ስለቆየሁ
ዛሬ ቁጭት ልቤን አሰቃየው
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
ወየው ወየው ወይኔ እኔ ሰውየው ወይኔ እኔ
Written by: Abdu Kiar Kahssay