Credits
PERFORMING ARTISTS
Abdu Kiar
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Dawit Tilahun
Songwriter
Lyrics
ሰላም ነሽ ወይ ጤና ድምጽሽ ጠፋ ምነው?
ተስማማሽ ወይ ኑሮ አገሩስ እንዴት ነው?
እኔ አልቻልኩበትም በጣም አቅቶኛል
ዉብ አይንሽን እስካይ ጭንቅ ብሎኛል
ሰላም ነሽ ወይ ጤና ድምጽሽ ጠፋ ምነው?
ተስማማሽ ወይ ኑሮ አገሩስ እንዴት ነው?
እኔ አልቻልኩበትም በጣም አቅቶኛል
ዉብ አይንሽን እስካይ ጭንቅ ብሎኛል
(ጊዜ ጌታ) ስትጥል ስታነሳ
(ጊዜ ጌታ) ስትሰጥ ስትነሳ
(ጊዜ ጌታ) አደራ አደራ አደራ
(ጊዜ ጌታ) ጸሎቴን እንዳትረሳ
አቤት አቤት ደስታ ያኔ የነበረው
ምነው ተገናኝተን ዛሬም በደገምነው
ምነው ተገናኝተን ዛሬም በደገምነው
እንባ ይቅር እንባ አታልቅሽ የኔ እናት
ዉብ አይንሽን ላዘን እሱ መች ፈጠራት
ዉብ አይንሽን ላዘን እሱ መች ፈጠራት
እኔ አላማርርም ተለያየን ብዬ
ሳይደግስ አይጣላም አይዞሽ እናትዬ
ደሞስ አማርሬ እኔ ምን ላመጣ
ለኔ ብሎ አይሮጥም ያው ነው ጊዜ ጌታ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ስትጥል ስታነሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ስትሰጥ ስትነሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) አደራ አደራ አደራ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ጸሎቴን እንዳትረሳ
በፍቅር በደስታ ስንቱን አሳልፈን
አይመስለኝም ነበር 'ምንኖር ተለያይተን
አይመስለኝም ነበር ምንኖር ተለያይተን
ሁሌ የማፈቅረው ሳቅ ጨዋታሽ ቀርቶ
የኔ እናት ቁጣሽም ይታየኛል ጎልቶ
የኔ እናት ቁጣሽም ይታየኛል ጎልቶ
ግን አላማርርም ተለያየን ብዬ
ሳይደግስ አይጣላም አይዞሽ እናትዬ
ደሞስ አማርሬ እኔ ምን ላመጣ
ለኔ ብሎ አይሮጥም ያው ነው ጊዜ ጌታ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ስትጥል ስታነሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ስትሰጥ ስትነሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) አደራ አደራ አደራ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ጸሎቴን እንዳትረሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ስትጥል ስታነሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ስትሰጥ ስትነሳ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) አደራ አደራ አደራ
(ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ) ጸሎቴን እንዳትረሳ
Written by: Dawit Tilahun

