Lyrics

ሁለመና ቆንጆ ሁለመና ፍቅር ኮከብ ነሽ ለሰማይ አልማዝ ነሽ ለምድር ከአይን ያውጣሽ እያልኩኝ ልደብቅሽ ስጥር ደግሞ ለብሰሽ ወጣሽ ብቅ አልሽ ወይ ለተዓምር አኮራሽን አስመካሽኝ አምረሽ ተውበሽ ታየሽልኝ የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባሳረረኝ የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባሳረረኝ እንኳን ትንፋሽሽ ሳቅሽ ይሞቃል ከቆምሽበት ምድር ፍቅር ይፈልቃል ሀገርሽ ጥጋብ አፈሩ ብርቅ ቢቀምሱት ስኳር ቢያነጥሩት ወርቅ ፈዋሽ መድኃኒት ፍቅርሽ ቢታደል ቢቆረጥ ፃድቅ ቢረጩት ፀበል በአይኔ ተገብኩሽ አልበላም ይቅር መቼም አይርበኝ ፆም ውዬ ባድር ባትዘጋጂ ባትለብሺ እንደሰው (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) የሰራ አካልሽ መች መልክ አነሰው (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) የፍቅር ፈትል የፍቅር ኩታ (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) ልከናነብሽ ጠዋት እና ማታ (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) የጥማቴ ፈዋሽ የርሀቤ ገበታ የቀን ምሳዬ ነሽ እራቴ ለማታ ከአፌ ማልነጥልሽ ከከንፈሬ ኬላ ከምላሴ ቁጭ በይ የኔ ከረሜላ ነይ ነይ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ ሜንታ ከረሜላ ደስታ ከረሜላ የኔ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ ሁለመና ቆንጆ ሁለመና ፍቅር ወይ አይኔ ወይ አይኔ መርጦ አገኘሽ ከሀገር ከአይን ያውጣሽ እያልኩኝ ልደብቅሽ ስጥር ደግሞ ለብሰሽ ወጣሽ ብቅ አልሽ ወይ ለተዓምር አስመካሽኝ አኮራሽኝ አምረሽ ተውበሽ መጣሽልኝ የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባሳረረኝ የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባደበነኝ ሲወራም የለው ሲመርጡም አላይ ልቤም ሰው የለው አይኔም ከአንቺው ላይ በእጅ አትነኪ በከንፈር ብቻ የጠዋት ዕድልሽ መፈቀር ብቻ ምግባረ ሰናይ ፀባየ ምቹ የተመረጥሽው ከቆንጆዎቹ የሰም እና ወርቅ የቅኔ ሚስጥር የመስተዋድድ የመስተፋቅር ልብሽ የአንበሳ ቁጣሽ የነብር (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) ሁሌ አንበርካኪ ጀግናን በፍቅር (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) የተወርዋሪ የኮከብ ጨረር (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) ቀልቤ ከአንቺው ጋር ሌት ያድራል ሲበር (የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው) በከንፈሬ ስሜሽ እቴ ሙች አረካም ይዜሽ ልጥፋ ከሀገር የኔ አመለ መልካም በወረት ተቀማሽ የአምሮት ፍቱን መልዐክ ለጠዐም የቀመሙሽ ሜንታ ከረሜላ ነይ ነይ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ ሜንታ ከረሜላ ደስታ ከረሜላ የኔ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ
Writer(s): Neway Debebe Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out